Appointment

Sign up for an appointment

It just takes a few minutes to sign up and get fast, easy access to care, 24/7. No need for your insurance card yet.


በኢትዮጵያ በግሉ የጤና ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነው “የኒውክለር ህክምና” ማዕከል ተከፈተ።

ኢትዮጵያ በግሉ የጤና ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነው “የኒውክለር ህክምና” ማዕከል ተከፈተ

የህክምና ዘረፍ 18 አመታትን ያሰቆጠረው ፓዮኒር ዲያግኖስቲክስ ማዕከልና ረዳት ሄልዝ ኬር ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፤ በኢትዮጵያ በግሉ የጤና ዘርፍ የመጀመሪያ የሆነውን የኒውክለር ህክምና ማዕከል ከፈተ።

ማእከሉ በ #አዲስ_አበባ አራት ኪሎ አካባቢ አርሾ ሀገፃ ላይ አግለግሎት መስጠት ጀምሯል። በአሁኑ ወቅት በመንግስት ሆስፒታል የኒውክለር ህክምና አገልግሎት በለመጀመሩ ፓዮኒር ዲያግኖስቲክስ ማዕከል በብቸኝነት አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል ተብሏል።

ማዕከሉ ቅዳሜ ባካሄደው የመክፈቻ ስነ ስርዓት፤ በኢትዮጵያ የኒውክለር ህክምና መጀመሩ ለህክምናው ወደ ውጭ አገር በመሄድ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጭ ይቀንሳል ተብሏል።

የመክፈቻ ስነ ስርዓቱ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ በኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተጽዕኖዎች እየጨመሩ መምጣቱን ጠቅሰው፤ የኒውክለር ህክምና በሽታዎችን ከመቆጣጠር፣ ከማከም እና ህመሞችን ከመቀነስ አንጻር ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።

“የኒውክለር ህክምና በግሉ ዘርፍ ተገንብቶ ማየት ለአገራችን ትልቅ ግብዓት ነው” ያሉት ሚንስትሯ፤ ከፍተኛ ወጪና ድካም በመቀነስ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ሚና አለውም ብለዋል።

ዶ/ር መቅደስ አክለውም በሶስት የመንግስት ሆስፒታሎች የኒውክለር ህክምና አገልግሎት ለማስጀምር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኒዩክለር ህክምና ማለት መጠነኛ ጨረር ያላቸው ጨረር አመንጭ መድኃኒቶችን በመጠቀም የሚደረግ የምርመራ እና የህክምና አይነት መሆኑን ነው። እያንዳንዱን የሰውነት አሰራርን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናት ኬሚካሎችን በማዘጋጀት ያሉበትን ደረጃ የሚለይ የህክምና መሳሪያ ነው።

ህክምናው በኢትዮጵያ ከ 1970ዎቹ ጀምሮ አገልግሎት ላይ የነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ አገልግሎቱ ተቋረጦ ቆይቷል። አሁን ላይ በፓዮኒር ዲያግኖስቲክስ ማዕከልና ረዳት ሄልዝ ኬር ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፤ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒዩክለር ህክምና ማዕከል አቋቁሞ በብቸኝነት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *